Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 7:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ዕጣንም የተሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወርቅ ሙዳይ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ዕጣን የተሞላበት አንድ ከወርቅ የተሠራ ዐሥር ሰቅል የዕጣን መያዣ፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዕጣንም የተሞላ ሚዛኑ አሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወርቅ ጭልፋ፤

See the chapter Copy




ዘኍል 7:14
13 Cross References  

ከጨረሱም በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ወደ ዮዳሄ አመጡ፤ በገንዘቡም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ዕቃዎች ማለትም ለአገልግሎትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚውሉ ዕቃዎች እንደዚሁም ጭልፋዎችና ሌሎች የወርቅና የብር ዕቃዎችም ተሠሩ። ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ይቀርብ ነበር።


ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት መኰስተሪያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።


ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ጽዋዎችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ጭልፋዎችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።


“በገጸ ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ይዘርጉበት፤ በላዩም ላይ ወጭቶች፣ ጭልፋዎች፣ ጽዋዎች፣ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች እንዲሁም ሁልጊዜ ከዚያ የማይታጣውን ኅብስት ያስቀምጡ።


የጠረጴዛውን ዕቃዎች ይኸውም ዝርግ ሳሕኖችን፣ ድስቶችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን እንዲሁም የመጠጥ መሥዋዕቱ ማፍሰሻ የሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠሯቸው።


ለመብራት የወይራ ዘይት፣ ለቅብዐ ዘይቱና ለጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፤


ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣


ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣


ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣


ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣


Follow us:

Advertisements


Advertisements