Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 6:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ ‘ድንገት ሰው አጠገቡ ሞቶ ለእግዚአብሔር የተለየበትን ጠጕሩን ቢያረክስበት፣ በሚነጻበት ዕለት ማለት በሰባተኛው ቀን ጠጕሩን ይላጭ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት እርሱም የተቀደሰውን ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጫል፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨዋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “በድንገት አንድ ሰው በአጠገቡ ቢሞት፥ የተቀደሰውን ራሱንም ቢያረክስ፥ በሰባተኛው ቀን ራሱን ይላጭ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ሰውም በአ​ጠ​ገቡ ድን​ገት ቢሞት የራሱ ብፅ​ዐት ይረ​ክ​ሳል፤ እርሱ በሚ​ነ​ጻ​በት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ይላ​ጨው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የተለየውንም ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨው።

See the chapter Copy




ዘኍል 6:9
11 Cross References  

“ ‘ከዚያም ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጨው፤ ጠጕሩንም ወስዶ ከኅብረቱ መሥዋዕት ሥር በሚነድደው እሳት ውስጥ ይጨምረው።


ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ብዙ ቀን በቆሮንቶስ ተቀመጠ፤ ከዚያም ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋራ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለትም ስለ ነበረበት ክንክራኦስ በተባለ ቦታ ራሱን ተላጨ።


በሰባተኛውም ቀን ጠጕሩን በሙሉ ይላጭ፤ ራሱን፣ ጢሙን፣ ቅንድቡንና ሌላውንም ጠጕር ሁሉ ይላጭ። ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።


ሰባቱ ቀንም ሊፈጸም ሲቃረብ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት አይሁድ ጳውሎስን በቤተ መቅደስ ባዩት ጊዜ፣ ሕዝቡን ሁሉ አነሣሥተው ያዙት፤


“የሚነጻው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ጠጕሩን በሙሉ ይላጭ፤ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ በሥርዐቱም መሠረት ንጹሕ ይሆናል። ከዚህም በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል፤ ነገር ግን ሰባት ቀን ከድንኳኑ ውጭ ይቈይ።


ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።


ወደ ቤትህ ውሰዳት፤ ጠጕሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቍረጥ።


በመቅደሱ ለማገልገል፣ ወደ መቅደሱ ውስጠኛው አደባባይ በሚገባበት ቀን፣ ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት ያቅርብ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements