Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 26:57 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ በጌርሶን በኩል፣ የጌርሶናውያን ጐሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 ከሌዋውያን ነገድ ተወላጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። የእነርሱም ዘሮች ሊብኒ፥ ኬብሮን፥ ማሕሊ፥ ሙሴ፥ ቆሬና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። ቀዓትም አሞራምን ወለደ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 የሌዊ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ከጌ​ድ​ሶን የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከቀ​ዓት የቀ​ዓ​ታ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ራሪ የሜ​ራ​ራ​ው​ያን ወገን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን።

See the chapter Copy




ዘኍል 26:57
12 Cross References  

የሌዊ ልጆች፦ ጌርሶን፣ ቀዓት እና ሜራሪ ናቸው።


የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌርሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።


የሌዊ ነገድ ቤተ ሰቦች ግን ከሌሎች ጋራ ዐብረው አልተቈጠሩም፤


ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሌዋውያኑ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ አልተቈጠሩም።


እያንዳንዱም ርስት በትልልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።”


የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ።


“ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው።


የሌዊ ልጆች ስም ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements