Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 9:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለመሆኑ፣ ‘ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል’ ከማለትና ‘ተነሥተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀልላል?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ‘ኃጢአቶችህ ተሰርየውልሃል’ ከማለትና ‘ተነሣና ሂድ’ ከማለት የትኛው ይቀላል?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ለመሆኑ ‘ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል’ ከማለትና ‘ተነሥተህ ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ‘ኀጢአትህ ተሰረየችልህ’ ከማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ከማለት ማናቸው ይቀላል?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?

See the chapter Copy




ማቴዎስ 9:5
15 Cross References  

ይህ የምታዩትና የምታውቁት ሰው የበረታው በኢየሱስ ስም በማመን ነው፤ ሁላችሁም እንደምታዩት ፍጹም ፈውስ እንዲያገኝ ያደረገው የኢየሱስ ስምና በርሱ አማካይነት የሚገኘው እምነት ነው።


ጴጥሮስም፣ “ኤንያ ሆይ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣና መኝታህን አንጥፍ” አለው። ኤንያም ወዲያውኑ ብድግ አለ።


በዚያም ሰዎች አንድ ሽባ ሰው በቃሬዛ ተሸክመው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አይዞህ አንተ ልጅ፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።


ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ ነው” ብሎ፣ ሽባውን፣ “ተነሣ! ቃሬዛህን ይዘህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።


ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።


ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ፣ “አንተ ሰው፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።


ኢየሱስም ሴቲቱን፣ “ኀጢአትሽ ተሰርዮልሻል” አላት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements