Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 27:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የካህናት አለቆች ብሩን አንሥተው፣ “የደም ዋጋ ስለ ሆነ ወደ መባ ልንጨምረው አይፈቀድም” አሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሊቀ ካህናቱም ብሩን አንሥተው “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አይፈቀድም” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የካህናት አለቆች ሠላሳውን ጥሬ ብር አንሥተው “ይህ ገንዘብ የደም ዋጋ ስለ ሆነ ከቤተ መቅደስ መባ ጋር ልንቀላቅለው አይፈቀድም” አሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም፤” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው፦ የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 27:6
8 Cross References  

ለዝሙት ዐዳሪ ሴት ወይም ለወንደቃ የተከፈለውን ዋጋ ለማንኛውም ስእለት አድርገህ ለመስጠት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አታምጣ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።


አይሁድም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ሮማዊው ገዥ ግቢ ይዘውት ሄዱ፤ ጊዜውም ማለዳ ነበር። አይሁድም ፋሲካን መብላት እንዲችሉ፣ ላለመርከስ ወደ ገዥው ግቢ አልገቡም።


እናንተ የታወራችሁ መሪዎች፤ ትንኝን አጥርታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ።


“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።


ስለዚህ ይሁዳ ብሩን በቤተ መቅደስ ውስጥ ወርውሮ ወጣ፤ ሄዶም ራሱን ሰቅሎ ሞተ።


ተመካክረውም ለእንግዶች የመቃብር ስፍራ እንዲሆን በገንዘቡ የሸክላ ሠሪውን ቦታ ገዙበት።


እናንተ ግን አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን፣ ከእኔ ማግኘት የሚገባችሁን ርዳታ ሁሉ ቍርባን፣ ይኸውም መባ እንዲሆን ሰጥቻለሁ ቢላቸው፣


Follow us:

Advertisements


Advertisements