Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 2:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “የልቅሶና የብዙ ዋይታ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና መጽናናትን እምቢ አለች።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “ራሔል ለልጆችዋ ስታለቅስ፥ የዋይታና፥ የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ልጆችዋም በሕይወት ስለሌሉ ለመጽናናት እምቢ አለች።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና።”

See the chapter Copy




ማቴዎስ 2:18
12 Cross References  

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ ከራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፣ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።”


የበኵር ልጇን ለመውለድ እንደምታምጥ፣ በወሊድ እንደምትጨነቅ ሴት ድምፅ ሰማሁ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ትንፋሽ ዐጥሯት ስትጮኽ፣ እጇን ዘርግታ፣ “ወዮልኝ! ተዝለፈለፍሁ፣ በነፍሰ ገዳዮች እጅ ወደቅሁ!” ስትል ሰማሁ።


እርሱም በፊቴ ዘረጋው፤ መጽሐፉም ከፊትና ከኋላው የሰቈቃ፣ የልቅሶና የዋይታ ቃላት ተጽፎበት ነበር።


ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “ብላቴናው ጕድጓድ ውስጥ የለም፤ የት አባቴ ልሂድ?” አለ።


ከዚያም ተመለከትሁ፤ አንድ ንስር በሰማይ መካከል ይበርር ነበር፤ በታላቅ ድምፅም፣ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚነፉ፣ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” ሲል ሰማሁ።


ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?


አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጕድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።


በዚህም በነቢዩ በኤርምያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፤


በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements