Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 14:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምክንያቱም ዮሐንስ፣ “እርሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዮሐንስ “እርሷ ለአንተ ትሆን ዘንድ ተገቢ አይደለም” ይለው ነበርና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ዮሐንስ ለሄሮድስ፦ “የወንድምህን ሚስት እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም!” ብሎት ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዮሐንስ “እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም፤” ይለው ነበርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዮሐንስ፦ እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም ይለው ነበርና።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 14:4
12 Cross References  

“ ‘ማንኛውም ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ አድራጎቱ ርኩሰት ነው፤ ወንድሙን አዋርዷልና፣ ያለ ልጅም ይቀራሉ።


“ ‘ከወንድምህ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ ወንድምህን ያዋርዳል።


ዮሐንስ ሄሮድስን፣ “የወንድምህን ሚስት ታገባት ዘንድ ሕግ ይከለክልሃል” ይለው ነበርና።


ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።


ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰውየውን ገደልኸው፤ ደግሞ ርስቱን ልትወስድ?’ ከዚያም እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ውሾች እንዲሁ ይልሱታል!’ ”


ከዚያም ናታን፣ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤


ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።


ነቢዩ ኤርምያስ ይህን ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements