Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 3:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሸለቆው ሁሉ ይሞላል፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማው መንገድ ቀና፣ ወጣ ገባውም ጐዳና ለጥ ያለ ሜዳ ይሆናል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጐድጓዳው ሁሉ ይሙላ፤ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማማውም መንገድ ቀና ይሁን፤ ሸካራውም መንገድ የተስተካከለ ይሁን፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጐድጓዳው ቦታ ሁሉ ይደልደል! ተራራና ኰረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል! ጠማማው መንገድ ይቅና! ሻካራውም መንገድ ይስተካከል!

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጐድ​ጓ​ዳው ሁሉ ይምላ፤ ተራ​ራ​ውም፥ ኮረ​ብ​ታ​ውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ሰን​ከ​ል​ካ​ላ​ውም የቀና ጥር​ጊያ ይሁን፤ ወጣ ገባው መን​ገ​ድም ይስ​ተ​ካ​ከል።

See the chapter Copy




ሉቃስ 3:5
11 Cross References  

ዕውሮችን በማያወቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ። ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ። ይህን አደርጋለሁ፤ አልተዋቸውም።


ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማው ምድር ይስተካከላል፤ ወጣ ገባውም ለጥ ያለ ሜዳ ይሆናል።


ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ።


‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችን እደለድላለሁ፤ የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ።


የዱር ዛፎች ሁሉ ረዥሙን ዛፍ፣ ዝቅ ዝቅ ያለውንም ዛፍ ከፍ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ የለመለመውን ዛፍ አደርቃለሁ፤ ደረቁንም አለመልማለሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔው አደርገዋለሁ።’ ”


ዝቅ ያለው ወንድም ከፍ በማለቱ ይመካ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements