Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 12:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ዐምስት ድንቢጦች በዐሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዲቷ እንኳ በእግዚአብሔር ዘንድ አትዘነጋም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አምስት ድንቢጦች በዐሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱ አንዲቱ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “አምስት ድንቢጦች በዐሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱ አንድዋ እንኳ በእግዚአብሔር ፊት የተረሳች አይደለችም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አም​ስት ወፎች በሁ​ለት ሻሚ መሐ​ለቅ ይሸጡ የለ​ምን? ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ስን​ኳን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አት​ረ​ሳም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አምስት ድንቢጦች በአሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም።

See the chapter Copy




ሉቃስ 12:6
8 Cross References  

ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ማከማቻ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?


በአንድ ሳንቲም ከሚሸጡት ሁለት ድንቢጦች አንዲቷ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ ምድር ላይ አትወድቅም።


ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።


“እስኪ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፤ አይለፉም፤ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነርሱ እንደ አንዷ አልለበሰም።


አንዲት ምስኪን መበለት ግን ከአንድ ሳንቲም የማይበልጡ ሁለት የናስ ሳንቲሞች አስገባች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements