Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 4:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እኛ እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን እንዳደረቀው ሁሉ፣ እናንተም እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ወንዝ በፊታችሁ አደረቀው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ ጌታ የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አምላካችን እግዚአብሔር እስክንሻገር ድረስ አስቀድሞ ለእኛ የቀይ ባሕርን እንዳደረቀልን፥ ለእናንተም የዮርዳኖስን ወንዝ እስክትሻገሩ ድረስ ውሃ አድርቆ ያሻገራችሁ መሆኑን ንገሩአቸው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ከፊ​ታ​ችን እን​ዳ​ደ​ረቀ እን​ዲሁ እስ​ክ​ን​ሻ​ገር ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ ከፊ​ታ​ችን አደ​ረቀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 4:23
8 Cross References  

ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔር ሌሊቱን በሙሉ ብርቱ የምሥራቅ ነፋስ አስነሥቶ ባሕሩን ወደ ኋላ በማሸሽ ደረቅ ምድር አደረገው፤ ውሃውም ተከፈለ።


በባሕር ውስጥ መንገድ፣ በማዕበል ውስጥ መተላለፊያ ያበጀ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤


ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።


በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው።


አንተ በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ገዛ ሕዝብህ እንደ እስራኤል፣ ስምህን በማወቅ እንዲፈሩህ፣ የሠራሁትም ይህ ቤት ስምህ የሚጠራበት ቤት መሆኑን እንዲያውቁ ባዕዱ ሰው የሚጠይቅህን ሁሉ አድርግ።


የፈርዖን ፈረሶች፣ ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሃ በላያቸው ላይ መለሰባቸው፤ እስራኤላውያን ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተሻገሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements