Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 24:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በፊታችሁ ተርብ ላክሁ፤ ይህም እነርሱንና ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ጭምር ከፊታችሁ አሳደደ፤ ይህ ደግሞ በራሳችሁ ሰይፍና ቀስት ያደረጋችሁት አይደለም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በሰይፍህም በቀሥትህም ሳይሆን በፊታችሁም ተርብ ሰድጄ ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት ከፊታችሁ አሳደዳቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ እንዳደረግሁት አስቀድሜ ከፊታችሁ ያባረራቸውን ተርብ ሰደድኩባቸው፤ ይህ በእናንተ ሰይፍ ወይም በእናንተ ቀስት የሆነ አይደለም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በፊ​ታ​ች​ሁም ተርብ ሰደ​ድሁ፤ በሰ​ይ​ፍ​ህም፥ በቀ​ስ​ት​ህም ሳይ​ሆን ዐሥራ ሁለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ነገ​ሥ​ታት ከፊ​ታ​ችሁ አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በፊታችሁም ተርብ ሰደድሁ፥ በሰይፍህም በቀሥትህም ሳይሆን ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት ከፊታችሁ አሳደዳቸው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 24:12
13 Cross References  

ይልቁንም አምላክህ እግዚአብሔር በሕይወት ተርፈው፣ ከአንተ የተደበቁት እንኳ እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ተርብ ይሰድድባቸዋል።


ኤዊያውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን ከመንገድህ ለማስወጣት ተርብን በፊትህ እሰድዳለሁ።


“ድንበርህን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድረ በዳው እስከ ወንዙ ድረስ አደርገዋለሁ፤ በምድሪቱም ላይ የሚኖሩትን ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም አሳድደህ ከፊትህ ታስወጣቸዋለህ።


መሬቱን መነጠርህላት፤ እርሷም ሥር ሰድዳ አገሩን ሞላች።


ስለዚህም እስራኤል በአሞራውያን ምድር ተቀመጠ።


ሙሴ ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ከላከ በኋላ እስራኤላውያን በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አባረሯቸው።


ይህም ከግብጽ በወጡ ጊዜ በሙሴና በእስራኤላውያን ድል በተደረገው፣ በሐሴቦን በነገሠው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ በቤተ ፌጎር አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ነው።


ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን፣ የርሱን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የዐግን፣ የሁለቱን አሞራውያን ነገሥታት ምድር ርስት አድርገው ወሰዱ።


እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው፣ እነዚህንም ያጠፋቸዋል።


ከግብጽ በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀ፣ እናንተም ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ፈጽሞ ያጠፋችኋቸውን ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት፣ ሴዎንንና ዐግን ምን እንዳደረጋችኋቸው ሰምተናል።


ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።


የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፣ የባሳንን ንጉሥ ዐግን፣ የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements