Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 22:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ ሀብት ይዛችሁ ማለትም አያሌ የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ናስና ብረት እንዲሁም ቍጥሩ እጅግ የበዛ ልብስ ይዛችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ ከጠላት የተገኘውንም ይህን ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋራ ተካፈሉት” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንዲህም አላቸው፦ “በብዙ ሀብት እጅግም ብዙ በሆነ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ እጅግም ብዙ በሆነ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንዲህም አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን በምርኮ ያገኛችሁትን ብዙ ከብት፥ ብር፥ ወርቅ፥ ነሐስ፥ ብረትና ብዙ ልብሶች ይዛችሁ ወደ መኖሪያችሁ ልትመልሱ ስለ ሆነ ከጠላቶቻችሁ በምርኮ ያገኛችሁትን ምርኮ ከዘመዶቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “በብዙ ብል​ጥ​ግና፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ከብት፥ በብ​ርም፥ በወ​ር​ቅም፥ በና​ስም፥ በብ​ረ​ትም፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ምርኮ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር ተካ​ፈሉ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፥ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 22:8
12 Cross References  

ምርኮውንም ለሁለት ከፍላችሁ በጦርነቱ ለተካፈሉት ወታደሮችና ለቀረው ማኅበረ ሰብ አከፋፍሉት።


በቀኝ እጇ ረዥም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።


የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋራ የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋራ አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።”


ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ፤ ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቷልና።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።


“የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤ በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ።


እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ መላው ይሁዳም ስጦታ ለኢዮሣፍጥ አመጣለት፤ ከዚህ የተነሣም ታላቅ ብልጽግናና ክብር አገኘ።


ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፣ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፣ ይጠጡና ይዘፍኑ፣ ይጨፍሩም ነበር።


ሕዝቅያስ እጅግ ብዙ ሀብትና ክብር ነበረው፤ ከዚህ የተነሣም ለብሩ፣ ለወርቁ፣ ለከበሩት ዕንቍዎቹ፣ ለቅመማ ቅመሞቹ፣ ለጋሻዎቹና ለተለያዩ ውድ ዕቃዎቹ ሁሉ ግምጃ ቤቶችን ሠራ።


ከብቶቻቸው በገለዓድ ምድር በዝተው ስለ ነበር፣ በምሥራቅ በኩል ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ የሚገኘውን ምድር ያዙ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements