Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 22:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “እኛም ‘እንነሣና መሠዊያ እንሥራ፤ የምንሠራው መሠዊያ ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ማቅረቢያ አይውልም’ ያልነው ለዚህ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለዚህም፦ ‘ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ያልሆነን መሠዊያ እንስራ አልን፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለዚህ እኛ የሠራነው መሠዊያ የሚቃጠል ወይም ሌላ መሥዋዕት ለማቅረብ አይደለም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ​ዚ​ህም መሠ​ዊያ እን​ሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ለቍ​ር​ባን አይ​ደ​ለም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለዚህም፦ መሠዊያ እንስራ አልን፥ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፥

See the chapter Copy




ኢያሱ 22:26
5 Cross References  

እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፤ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን በመካከላችን መለያ ድንበር ስላደረገው፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድርሻ የላችሁም።’ ስለዚህ ዘሮቻችሁ፣ የእኛ ዘር እግዚአብሔርን እንዳይፈራ ሊያደርጉ ይችላሉ።


በሌላም በኩል የሚቃጠል መሥዋዕታችንን፣ ሌላውን ቍርባናችንንና የኅብረት መሥዋዕታችንን ይዘን በተቀደሰው ስፍራ እግዚአብሔርን እንደምናመልክ መሠዊያው በእኛና በእናንተ እንዲሁም በሚቀጥሉት ትውልዶች መካከል ምስክር ይሆናል። ስለዚህ ወደ ፊት ዘሮቻችሁ ዘሮቻችንን፣ ‘ከእግዚአብሔር ዘንድ ድርሻ የላችሁም’ ሊሏቸው አይችሉም።


በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለእግዚአብሔር ዐምድ ይቆማል።


“በማደሪያው ድንኳን ፊት ካለው ከእግዚአብሔር ከአምላካችን መሠዊያ ሌላ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለእህል ቍርባን እንዲሁም ለሌላ መሥዋዕት ማቅረቢያ የሚሆን መሠዊያ በመሥራት ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ እናምፅን? እርሱን ማምለካችንንም እንተውን? ይህ ከእኛ ይራቅ!”


ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “እግዚአብሔር ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements