Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 2:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እርሷም፣ “ይሁን፤ ባላችሁት ተስማምቻለሁ” ስትል መለሰች። ከዚያም ሰደደቻቸው፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀይ ፈትሉንም በመስኮቷ ላይ አንጠለጠለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እርሷም እንዲህ አለች፦ “እንደ ቃላችሁ ይሁን፤” ከዚያም በኋላ በደኅና አሰናበተቻቸው እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እርስዋም በዚህ ተስማምታ ሸኘቻቸው፤ እነርሱም ከሄዱ በኋላ ቀዩን ገመድ በመስኮቱ ላይ አንጠለጠለች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እር​ስ​ዋም፥ “እንደ ቃላ​ችሁ ይሁን” አለች፤ አሰ​ና​በ​ተ​ቻ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም ሄዱ፤ ቀዩ​ንም ፈትል በመ​ስ​ኮቱ በኩል አን​ጠ​ለ​ጠ​ለ​ችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እርስዋም፦ እንደ ቃላችሁ ይሁን አለች፥ ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፥ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 2:21
6 Cross References  

እናቱም በዚያ የነበሩትን አገልጋዮች፣ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው።


“እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል።


ወደ ምድሪቱ በገባን ጊዜ፣ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወረድሽበት መስኮት ላይ አስረሽ ካንጠለጠልሽው፣ እንዲሁም አባትሽንና እናትሽን፣ ወንድሞችሽንና የአባትሽን ቤተ ሰዎች ሁሉ ወደ ቤትሽ ካመጣሻቸው ብቻ ነው።


እኛ የምናደርገውን ብትናገሪ ግን፣ ካስማልሽን መሐላ ነጻ እንሆናለን።”


እነርሱም ወጥተው ወደ ኰረብቶቹ ሄዱ፤ የሚከታተሏቸውም ሰዎች በየመንገዱ ሁሉ ላይ ፈልገውና ዐጥተው እስኪመለሱ ድረስ፣ ሦስት ቀን በዚያው ተሸሸጉ።


እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements