ኢያሱ 2:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ማንም ከቤትሽ ወጥቶ መንገድ ላይ ቢገኝ፣ ደሙ በራሱ ላይ ነው፤ እኛ አንጠየቅበትም፤ ነገር ግን ከአንቺ ጋራ ቤት ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ከተነካ የደሙ ባለዕዳ እኛ እንሆናለን። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፥ እኛም ንጹሐን እንሆናለን፤ ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን ማንም ሰው እጁን ቢጭንበት ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ማንም ከቤት ወጥቶ ቢገኝና ቢሞት ጥፋቱ የራሱ ይሆናል፤ እኛም በኀላፊነት አንጠየቅም፤ ከአንቺ ጋር በቤት ሳለ ማንም ሰው ጒዳት ቢደርስበት ግን በኀላፊነት ተጠያቂዎች ነን። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ ንጹሓን እንሆናለን፤ ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤትሽ ውስጥ ያለ ቢሞት ደሙ በእኛ ላይ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፥ እኛም ንጹሐን እንሆናለን፥ ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን አንድ እጅ ቢነካው ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል። See the chapter |