ኢያሱ 18:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በሰሜን ያለው ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ይነሣና የኢያሪኮን ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ፣ በስተ ምዕራብ ወዳለው ኰረብታማ ምድር በማምራት፣ እስከ ቤትአዌን ምድረ በዳ ይዘልቃል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፤ ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው አገር በኩል ወደ ምዕራብ ወጣ፥ መጨረሻውም በቤትአዌን ምድረ በዳ ነበረ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 በሰሜን በኩል የሚገኘውም ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ወንዝ ተነሥቶ ወደ ኢያሪኮ ሰሜን ሽቅብ ይወጣና በምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው ኮረብታማ አገር በኩል እስከ ቤትአዌን በረሓ ይደርሳል፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፤ ድንበሩም ከኢያሪኮ አዜብ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው ሀገር ወደ ባሕር ወጣ፤ መውጫውም የቤቶን ምድብራይጣስ ነበረ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፥ ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው አገር ወደ ምዕራብ ወጣ፥ መውጫውም በቤትአዌን ምድረ በዳ ነበረ። See the chapter |