Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 15:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፤ ስለዚህ ካሌብ ልጁን ዓክሳንን አጋባው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህም የካሌብ ወንድም ከሆነው ከቀናዝ የተወለደው ዖትኒኤል ያችን ከተማ ወግቶ ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የካ​ሌብ ወን​ድም የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያል ያዛት፤ ልጁን አክ​ሳ​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፥ ልጁንም ዓክሳን አጋባው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 15:17
9 Cross References  

እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ ግን የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው።


በዚህ ጊዜ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳንን ዳረለት።


የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።


የይሁዳም ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከዚያም የቄኔዛዊው የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ ስለ አንተና ስለ እኔ፣ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ የተናገረውን ታውቃለህ።


እንዲሁም የማድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።


እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸው ተከትለውታልና፣ ከቄኔዛዊው ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር አንዳቸውም አያዩዋትም።’


ካሌብ፣ “ቂርያትሤፍርን ወግቶ ለሚይዝ ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” አለ።


የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ ጎቶንያል፣ ሠራያ። የጎቶንያል ወንዶች ልጆች፤ ሐታት፣ መዖኖታይ።


በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ ዐሥራ ሁለተኛው የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተ ሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements