ኢያሱ 14:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ዐብረውኝ ወደዚያ የወጡት ወንድሞቼ ግን፣ የሕዝቡ ልብ በፍርሀት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ ሆኖም እኔ አምላኬን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቤ ተከተልሁት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን ጌታን ፈጽሜ ተከተልሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ከእኔ ጋር ሄደው የነበሩ ሰዎች ግን የሕዝቡ ልብ በፍርሃት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ እኔ ግን ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በታማኝነት ታዛዥ ሆኛለሁ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞች ግን የሕዝቡን ልብ አስካዱ፤ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ እከተለው ዘንድ ተመለስሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ አቀለጡ፥ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ። See the chapter |