Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 12:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣ ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቷል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በሐሴቦን የተቀመጠው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፥ ይገዛ የነበረው በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ሲሆን፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በሐሴቦን ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ነበር፤ ግዛቱም የገለዓድን እኩሌታ በማጠቃለል፥ በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከምትገኘው ከዓሮዔር ተነሥቶ በዚያ ሸለቆ መካከል ያለችውን የዐሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ይደርስ ነበር፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በሐ​ሴ​ቦን የተ​ቀ​መ​ጠው፥ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ ከሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን እኩ​ሌታ እስከ ኢያ​ቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፥

See the chapter Copy




ኢያሱ 12:2
12 Cross References  

በዚያች ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ፤ ሁለቱን ሚስቶቹን እንዲሁም ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንድ ልጆቹን ይዞ በያቦቅ መልካ ተሻገረ።


የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፣ የባሳንን ንጉሥ ዐግን፣ የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፤


“በሩቅ የሚገኙትን ድንበሮች እንኳ ሳይቀር፣ መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው። የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፣ የባሳን ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።


ከአርኖን እስከ ያቦቅ፣ ከምድረ በዳው እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ያለውን የአሞራውያንን ድንበር በሙሉ ወረሱ።


የአሞናውያንም ንጉሥ ለዮፍታሔ መልእክተኞች፣ “ይህን ያደረግሁት እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ በአርኖንና በያቦቅ ወንዞች መካከል ያለውንና እስከ ዮርዳኖስ ያለውን አገሬን ስለ ወሰዱብኝ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” አላቸው።


የኢዩኤል ልጅ፣ የሽማዕ ልጅ፣ የዖዛዝ ልጅ ቤላ። እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ።


አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።


ይህ የሆነው በሐሴቦን ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንና በአስታሮት ይገዛ የነበረውን የዐግን ንጉሥ ባሳንን በኤድራይ ድል ካደረገ በኋላ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements