Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 11:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ቈረጠ፤ ሠረገሎቻቸውንም አቃጠለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢያሱም ጌታ እንዳዘዘው በእነሱ ላይ አደረገባቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቈረጠ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢያሱም በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። ይኸውም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ቈረጠ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢያ​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገባቸው፥ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቈረጠ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 11:9
6 Cross References  

እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው።


ወደ ሸንጓቸው አልግባ፤ ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤ በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤ የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል።


ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኞችና ሃያ ሺሕ እግረኞች ማረከበት። ቍጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በእናንተ ላይ ተነሥቼባችኋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁን አቃጥዬ አጨሳለሁ፤ ደቦል አንበሶቻችሁን ሰይፍ ይበላል፤ የምትበሉትን በምድር ላይ አልተውላችሁም፤ የመልእክተኞቻችሁም ድምፅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።”


“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements