Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 5:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አዳምም መቶ ሠላሳ ዓመት ሲኖር፥ እሱን የሚመስል፥ አምሳያው የሆነ፥ የልጅ አባት ሆነ፤ ሤት ብሎም ስም አወጣለት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልኩና በአምሳያው እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ሤት” የሚል ስምም አወጣለት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አዳ​ምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም እንደ ምሳ​ሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙ​ንም ሴት ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 5:3
15 Cross References  

አዳም እንደ ገና ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ሴት ብላ ጠራችው።


እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንን ምኞት እያረካን፣ መንገዱንም እየተከተልን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም የቍጣ ልጆች ነበርን።


ሥጋ ሁሉ አንድ አይደለም፤ የሰው ሥጋ አንድ ነው፤ የእንስሳት ሥጋ ሌላ ነው፤ የወፎችም ሥጋ ሌላ ነው፤ የዓሦችም ሥጋ ሌላ ነው።


ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቷል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤


ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደም መንፈስ ነው።


መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፤ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኀይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ የሚወለደው ቅዱሱ ሕፃን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።


ስወለድ ጀምሮ በደለኛ፣ ገና እናቴም ስትፀንሰኝ ኀጢአተኛ ነኝ።


ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፣ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ይችላልን?


ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹሕን ማን ሊያወጣ ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም!


የቃይንም ልጅ፣ የአርፋክስድ ልጅ፣ የሴም ልጅ፣ የኖኅ ልጅ፣ የላሜህ ልጅ፣


የምድራዊውን ሰው መልክ እንደ ለበስን፣ የሰማያዊውን ሰው መልክ ደግሞ እንለብሳለን።


ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ባረካቸው፤ በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው፦


ሴት ከተወለደም በኋላ፣ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements