Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዳንኤል 3:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 መኳንንቱ፣ ሹማምቱ፣ አገረ ገዦቹ፣ አማካሪዎቹ፣ የግምጃ ቤት ኀላፊዎቹ፣ ዳኞቹ፣ ሌሎች የሕግ ዐዋቂዎችና በየአውራጃው ያሉ ሹማምት ሁሉ ንጉሥ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ በዓል ተሰበሰቡ፤ በምስሉም ፊት ቆሙ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነዚህ ሁሉ ባለሥልጣኖች ለምረቃው በዓል በአንድነት ተሰብስበው በምስሉ ፊት ለፊት ቆሙ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፥ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፥ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፥ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ።

See the chapter Copy




ዳንኤል 3:3
11 Cross References  

የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ ዕቅዱን እንዲፈጽሙ፣ ደግሞም በአንድ ሐሳብ እንዲስማሙና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው እንዲሰጡ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነውና።


አንድ ሐሳብም አላቸው፤ ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ፤


አስተዋይ የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚሻ አንድም የለም።


ከዚያም መኳንንትን፣ ሹማምትን፣ አገረ ገዦችን፣ አማካሪዎችን፣ የግምጃ ቤት ኀላፊዎችን፣ ዳኞችን፣ ሌሎች የሕግ ዐዋቂዎችንና በየአውራጃው ያሉትን ሹማምት ሁሉ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ በዓል እንዲመጡ ጠራ።


ከዚያም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ የሚል ዐዋጅ ታወጀ፤ “ሕዝቦች ሆይ፤ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ሰዎች ሁሉ፤ እንድታደርጉ የታዘዛችሁት ይህ ነው፤


መኳንንቱ፣ ሹማምቱ፣ አገረ ገዦቹና የቤተ መንግሥት አማካሪዎችም በዙሪያቸው ተሰበሰቡ፤ እነርሱም እሳቱ ሰውነታቸውን እንዳልጐዳ፣ ከራሳቸውም ጠጕር አንዲቷ እንኳ እንዳልተቃጠለች አዩ፤ የመጐናጸፊያቸው መልክ አልተለወጠም፤ የእሳትም ሽታ በላያቸው አልነበረም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements