2 ሳሙኤል 5:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በዚያም ዕለት ዳዊት፣ “ኢያቡሳውያንን ድል ማድረግ የሚፈልግ፣ የዳዊት ጠላቶች ወደሚሆኑ፣ ‘ዐንካሶችና ዕውሮች’ ለመድረስ በውሃ መተላለፊያው ሽቅብ መውጣት አለበት” አለ። እንግዲህ፣ “ ‘ዐንካሶችና ዕውሮች’ ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም” ያሉት ለዚህ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በዚያም ዕለት ዳዊት፥ “ኢያቡሳውያንን መግደል የሚፈልግ፥ የዳዊት ጠላቶች ወደሚሆኑ፥ ‘አንካሶችና ዕውሮች’ ለመድረስ በውሃ መተላለፊያው ይውጣ” አለ። ለዚህም ነበር፥ “አንካሶችና ዕውሮች ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም” የተባለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በዚያን ቀን ዳዊት አንዲህ አለ፦ “ኢያቡሳውያንን የሚመታ ዳዊት በሚጠላቸው በዕውሮችና በአንካሶች ላይ አደጋ ለመጣል በውሃው መተላለፊያ ይውጣ፤” ስለዚህም ዕውሮችና አንካሶች ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም ተባለ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በዚያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያቡሴዎናውያንን የሚመታ ሁሉ፥ ዕውሮችንና አንካሶችን፥ የዳዊትንም ነፍስ የሚጠሉትን ሁሉ በሳንጃ ይውጋቸው” አለ። ስለዚህም፥ “ዕውርና አንካሳ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግቡ” ተባለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በዚያም ቀን ዳዊት፦ ኢያቡሳውያንን የሚመታ በውኃ መሄጃው ይውጣ፥ የዳዊትም ነፍስ የምትጠላቸውን ዕውሮችንና አንካሶችን ያውጣ አለ። ስለዚህም በምሳሌ፦ ዕውርና አንካሳ ወደ ቤት አይግቡ ተባለ። See the chapter |