Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 20:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዳዊት ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ ንጉሡም ቤቱን እንዲጠብቁ ትቷቸው የሄደውን ዐሥሩን ቁባቶቹን ወሰደ፤ በአንድ ቤትም ውስጥ እንዲጠበቁ አደረገ። ቀለብ ሰጣቸው፤ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ አልገባም ነበር፤ እነርሱም እስከ ሞቱበት ጊዜ ድረስ መበለት ሆነው፣ ለብቻቸው ተገልለው ተቀመጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊት ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በተመለሰ ጊዜ፤ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ትቶአቸው የሄደውን ዐሥሩን ዕቁባቶቹን ወሰደ፤ በአንድ ቤትም ውስጥ እንዲጠበቁ አደረገ። ቀለብ ሰጣቸው፤ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ አልገባም ነበር፤ እነርሱም እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ መበለት ሆነው፥ ለብቻቸው ተገልለው ተቀመጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ በደረሰ ጊዜ፥ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁለት ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥር ቊባቶቹን ወደ ሌላ ወስዶ በዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፤ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሰጣቸው አዘዘ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አልፈጸመም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው በቤት ተወስነው እንደ መበለቶች በመሆን ኖሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉ​ሡም ቤቱን ሊጠ​ብቁ የተ​ዋ​ቸ​ውን ዐሥ​ሩን ቁባ​ቶች ወስዶ ለጠ​ባቂ ሰጣ​ቸው፤ ቀለ​ብም ሰጣ​ቸው፤ ነገር ግን ወደ እነ​ርሱ አል​ገ​ባም፤ በቤ​ትም ተዘ​ግ​ተው እስ​ኪ​ሞቱ ድረስ መበ​ለ​ቶች ሆነው ተቀ​መጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ መጣ፥ ንጉሡም ቤቱን ሊጠብቁ የተዋቸውን አሥሩን ቁባቶች ወስዶ ለጠባቂ ሰጣቸው፥ ቀለብም ሰጣቸው፥ ነገር ግን ወደ እነርሱ አልገባም፥ በቤት ተዘግተው እስኪሞቱም ድረስ ባልቴቶች ሆነው ተቀመጡ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 20:3
4 Cross References  

ንጉሡ ከመላው ቤተ ሰቡ ጋራ ወጣ፤ ቤተ መንግሥቱንም እንዲጠብቁ ዐሥር ቁባቶች አስቀረ።


በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደ ተጋዘበትም እስር ቤት አስገባቸው።


ስለዚህ የእስራኤል ሰው ሁሉ ዳዊትን ከድቶ የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተለ። የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንሥቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው ሳይለዩ ዐብረውት ሄዱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements