Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 14:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም ንጉሡ ሴቲቱን፣ “እኔም ለምጠይቅሽ ነገር አንቺም መልሱን አትደብቂኝ” አላት። ሴቲቱም፣ “ንጉሥ ጌታዬ፤ ዕሺ ይናገር” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚያም ንጉሡ ሴቲቱን፥ “የምጠይቅሽን ነገር አንድም ሳትደብቂኝ መልሽልኝ” አላት። ሴቲቱም፥ “ንጉሥ ሆይ! ጠይቀኝ” አለችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ንጉሡም “አንድ ጥያቄ እጠይቅሻለሁ፤ አንቺም እውነቱን በሙሉ ንገሪኝ” አላት። እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! የፈለግኸውን ጠይቀኝ” አለችው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ንጉ​ሡም ለሴ​ቲቱ መልሶ፥ “የም​ጠ​ይ​ቅ​ሽን ነገር አት​ሰ​ው​ሪኝ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ይና​ገር” አለች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ንጉሡም ለሴቲቱ መልሶ፦ የምጠይቅሽን ነገር አትሰውሪኝ አላት። ሴቲቱም፦ ጌታዬ ንጉሥ ይናገር አለች።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 14:18
5 Cross References  

መኳንንቱ ከአንተ ጋራ እንደ ተነጋገርሁ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና፣ ‘ንጉሡን ምን እንዳልኸው፣ ንጉሡም ምን እንዳለህ ንገረን፤ ሳትደብቅ ንገረን፤ አለዚያ እንገድልሃለን’ ቢሉህ፣


ንጉሡ ሴዴቅያስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ልኮ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስተኛው በር አስመጣውና፤ “አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።


“አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ እግዚአብሔር አምላክህም ካንተው ጋራ ይሁን’ ትላለች።”


ንጉሡም፣ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ የለበትምን?” ሲል ጠየቃት። ሴቲቱም መልሳ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከተናገረው ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም የሚል ማንም የለም። አዎን ይህን እንዳደርግ ያዘዘኝና ይህም ሁሉ ቃል በእኔ በአገልጋይህ አንደበት እንዲነገር የላከኝ አገልጋይህ ኢዮአብ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements