Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 13:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አቤሴሎምም፣ “እንግዲያውስ ወንድሜ አምኖን ዐብሮን ይሂድ” አለው። ንጉሡም፣ “ዐብሯችሁ የሚሄደው ስለ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከዚያም አቤሴሎም፥ “እምቢ ካልህ እሽ ወንድሜ አምኖን አብሮን ይሂድ” አለው። ንጉሡም፥ “አብሮህ የሚሄደው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 አቤሴሎም ግን “መልካም ነው! አንተ መምጣት ካልፈቀድህ ወንድሜ አምኖን እንዲመጣ አትፈቅድለትምን?” ሲል ጠየቀ። ንጉሡም “እርሱስ ቢሆን ለምን ይመጣል?” ሲል ጠየቀው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወን​ድሜ አም​ኖን ከእኛ ጋር እን​ዲ​ሄድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “ከአ​ንተ ጋር ለምን ይሄ​ዳል?” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 አቤሴሎምም አንተ እንቢ ካልህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር እንዲሄድ እለምንሃለሁ አለ። ንጉሡም፦ ከአንተ ጋር ለምን ይሄዳል? አለው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 13:26
8 Cross References  

አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው፤ በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው፤ ይሁን እንጂ የተመዘዘ ሰይፍ ነው።


ኢዮአብም አሜሳይን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እንደ ምንድን ነህ?” አለው፤ ከዚያም አሜሳይን የሚስም መስሎ በቀኝ እጁ ጢሙን ያዘው።


አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፣ ኢዮአብ በቈይታ የሚያነጋግረው በመምሰል ዞር አድርጎ ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሲል፣ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።


ንጉሡም፣ “ልጄ ሆይ፣ ሁላችንም መሄድ የለብንም፤ ሸክም እንሆንብሃለን” ሲል መለሰለት። አቤሴሎም አጥብቆ ቢለምነውም ንጉሡ መሄድ አልፈለገም፤ ነገር ግን መርቆ አሰናበተው።


ነገር ግን አቤሴሎም አጥብቆ ስለ ለመነው፣ አምኖንና ሌሎቹ የንጉሡ ወንዶች ልጆች ሁሉ ዐብረውት እንዲሄዱ አደረገ።


ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤ በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል።


ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ብረት አነጥራቸዋለሁ፤ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት፣ ከዚህ የተለየ ምን ማድረግ እችላለሁ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements