Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 13:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ንጉሥ ዳዊት ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ንጉሥ ዳዊት ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ንጉሥ ዳዊት የሆነውን ነገር በሰማ ጊዜ በብርቱ ተቈጣ፤ [ነገር ግን ይወደው ስለ ነበርና የበኲር ልጁም ስለ ነበረ ልጁን አምኖንን ሊያሳዝነው አልፈለገም።]

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ንጉ​ሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ ሰማ፤ እጅ​ግም ተቈጣ፥ ነገር ግን የበ​ኵር ልጁ ነበ​ረና ስለ ወደ​ደው የል​ጁን የአ​ም​ኖ​ንን ነፍስ አላ​ሳ​ዘ​ነም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ንጉሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ነገር ግን የበኵር ልጁ ነበረና ስለ ወደደው የልጁን የአምኖን ነፍስ አላሳዘነም።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 13:21
10 Cross References  

የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም የተፈጸመውን ድርጊት እንደ ሰሙ ወዲያውኑ ከመስክ መጡ፤ ሴኬም መደረግ የማይገባውን አስነዋሪ ነገር በእስራኤል ላይ በመፈጸም፣ የያቆብን ልጅ ስለ ደፈረ ዐዘኑ፤ ክፉኛም ተቈጡ።


በምድሪቱ ላይ ያሉትን ክፉዎች ሁሉ፣ በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ፣ ከእግዚአብሔር ከተማ እደመስሳቸዋለሁ።


ስለዚህ ሰይፍ ለዘላለም ከቤትህ አይርቅም፤ እኔን አቃልለኸኛል፤ ሚስት እንድትሆንህም የኬጢያዊውን የኦርዮን ሚስት ወስደሃታልና።’


ዳዊት በዚያ ሰው ላይ እጅግ ተቈጥቶ ናታንን እንዲህ አለው፤ “ሕያው እግዚአብሔርን ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል!


ታዲያ በማደሪያዬ እንዲቀርብ ያዘዝሁትን መሥዋዕትና ቍርባን የናቃችሁ ለምንድን ነው? አንተና ልጆችህ ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቍርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር ከእኔ ይልቅ ልጆችህን የምታከብራቸው ስለ ምንድን ነው?’


ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ያ ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋራ ነበርን? እኅቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለ ሆነ፤ ነገሩን በልብሽ አትያዢው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች።


አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ ደግ አንዳች ቃል አልተናገረውም፤ ምክንያቱም አምኖን እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት ጠልቶት ነበር።


እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements