Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 13:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ያ ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋራ ነበርን? እኅቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለ ሆነ፤ ነገሩን በልብሽ አትያዢው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ወንድሟ አቤሴሎምም፥ “ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበርን? እኅቴ ሆይ፥ በይ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለሆነ፥ ነገሩን በልብሽ አትያዠው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ወንድምዋ አቤሴሎም ባያት ጊዜ “እኅቴ ሆይ! ወንድምሽ አምኖን አስነወረሽን? እባክሽ እንደዚህ አትበሳጪ፤ እርሱ ወንድምሽ ስለ ሆነ ለማንም አትናገሪ” አላት። ስለዚህ ትዕማር በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ከሰው የተለየች ብቸኛ ሆና ተቀመጠች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ወን​ድ​ም​ዋም አቤ​ሴ​ሎም፥ “ወን​ድ​ምሽ አም​ኖን ከአ​ንቺ ጋር ነበ​ርን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፤ ወን​ድ​ምሽ ነውና፤ ይህን ነገር ትና​ገሪ ዘንድ በል​ብሽ አታ​ስቢ” አላት። ትዕ​ማ​ርም በወ​ን​ድ​ምዋ በአ​ቤ​ሴ​ሎም ቤት መበ​ለት ሆና ተቀ​መ​ጠች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ወንድምዋም አቤሴሎም፦ ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበረን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፥ ወንድምሽ ነው፥ ይህን ነገር በልብሽ አትያዢው አላት። ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት ብቻዋን ተቀመጠች።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 13:20
7 Cross References  

ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።


ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤ በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል።


እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቍጥር ሠላሳ ሦስት ነው።


ሴኬም የተባለው የአገሩ ገዥ የኤዊያዊ የኤሞር ልጅ ባያት ጊዜ ይዞ በማስገደድ ደፈራት።


ትዕማርም በራሷ ላይ ዐመድ ነሰነሰች፤ ጌጠኛ ልብሷን ቀደደች፤ ከዚያም እጇን በራሷ ላይ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች።


ንጉሥ ዳዊት ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤


ንጉሡ ግን፣ “እዚያው እቤቱ ይሂድ፤ ዐይኔን ማየት የለበትም” አለ። ስለዚህም አቤሴሎም ወደ ቤቱ ሄደ፤ የንጉሡንም ፊት አላየም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements