Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 1:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ ዐዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ፤ ከሴት ፍቅርም ይልቅ ግሩም ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ፤ ከሴት ፍቅርም ይልቅ የበረታ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “ወንድሜ ዮናታን ሆይ! እኔ ስለ አንተ በጣም አዘንኩ፤ አንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ነበርክ። ፍቅርህ ለእኔ አስደናቂ ነበር፤ ይኸውም ከሴት ፍቅር የበረታ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ወን​ድሜ ዮና​ታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተ​ወ​ደ​ድህ ነበ​ርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅ​ርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፥ በእኔ ዘንድ ውድህ እጅግ የተለየ ነበር፥ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበረ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 1:26
7 Cross References  

ዮናታን ከፍቅሩ የተነሣ ዳዊት እንደ ገና እንዲምልለት አደረገ፤ ዳዊትን የሚወድደውም እንደ ራሱ አድርጎ ነበርና።


የሳኦል ልጅ ዮናታንም ዳዊት ወዳለበት ወደ ሖሬሽ ሄዶ፣ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው፤


ልጁ ከሄደ በኋላ፣ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር።


እንዲህ ሲል አስጠነቀቀው፤ “አባቴ ሳኦል ሊገድልህ አጋጣሚ እየፈለገ ነው፤ ነገ ጧት ተጠንቀቅ፤ ወደ አንድ መደበቂያ ቦታም ሂድ፤ በዚያም ቈይ።


“ኀያላኑ እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ከንቱ ይሁኑ!”


ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements