Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 1:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንዲሁም የቀስት እንጕርጕሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፏል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የይሁዳንም ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ እነሆ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የይሁዳም ሕዝብ ያጠኑት ዘንድ አዘዘ፤ ቅኔውም በያሻር መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፦

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የይ​ሁ​ዳ​ንም ልጆች ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ ይህ በጻ​ድ​ቃን መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 1:18
4 Cross References  

ስለዚህ ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ፣ ፀሓይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ፀሓይ በሰማዩ መካከል ቆመች፤ ለመጥለቅም ሙሉ ቀን ፈጀባት።


“በምድሪቱ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ እኔን ማክበር እንዲማሩ፣ ለልጆቻቸውም እንዲያስተምሩ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ሕዝቡን በፊቴ ሰብስብ” ባለኝ ጊዜ፣ በኮሬብ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቆማችሁበትን ዕለት አስታውሱ።


“ይሁዳ፣ ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤ እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል።


“እስራኤል ሆይ፤ ክብርህ በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል፤ ኀያላኑ እንዴት እንደዚህ ይውደቁ!


Follow us:

Advertisements


Advertisements