Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 7:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሳሙኤልንም፣ “አምላካችን እግዚአብሔር ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ስለ እኛ ወደ እርሱ መጸለይህን አታቋርጥ” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሳሙኤልንም፥ “አምላካችን ጌታ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ስለ እኛ ወደ እርሱ መጸለይህን አታቋርጥ” አሉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሳሙኤልንም፦ “ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር መጸለይን አታቋርጥ” አሉት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ከመ​ጮኽ ዝም አት​በል። እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ነ​ናል” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእስራኤልም ልጆች ሳሙኤልን፦ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ትጸልይልን ዘንድ አትታክት አሉት።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 7:8
7 Cross References  

ምናልባት ሕያው አምላክን ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የጦር አዛዡን ቃል እግዚአብሔር አምላክህ ይሰማ ይሆናል፤ እግዚአብሔር አምላክህም ሰምቶ ይገሥጸው ይሆናል፤ ስለዚህ አንተም በሕይወት ለተረፉት ቅሬታዎች ጸልይ።’ ”


ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።


ጽድቋ እንደ ማለዳ ወጋገን እስኪፈነጥቅ፣ ድነቷ እንደሚያንጸባርቅ ፋና እስኪታይ፣ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም።


እውነተኞች ነቢያት ከሆኑና በርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ካላቸው፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ ወደ ሰራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር እስኪ ይማልዱ!


ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ቀድሞ ብዙዎች ነበርን አሁን እንደምታየን ግን የቀረነው ጥቂት ነን፤ ስለዚህ እባክህ ልመናችንን ስማ፤ ለዚህ ለተረፈው ሕዝብ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements