Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 6:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ቤትሳሚስ አቅጣጫ ወደ ገዛ አገሩ የሚሄድ ከሆነ፣ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እግዚአብሔር ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፣ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤ አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ተመልከቱም፥ በድንበሩም መንገድ ወደ ቤትሳሚስ ቢወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እግዚአብሔር ነው፥ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 6:9
13 Cross References  

ከዚያም ከበኣላ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ሴይር ይታጠፍና ክሳሎን ተብሎ በሚጠራው በይዓሪም ኰረብታ ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ ቍልቍል ወደ ቤትሳሚስ በመውረድ ወደ ተምና ይሻገራል።


አንድ ካህን በአጋጣሚ በዚያው መንገድ ቍልቍል ሲወርድ አየውና ገለል ብሎ ዐለፈ።


ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤ ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።


ወሬ ነጋሪው ወጣትም እንዲህ አለ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ የሠረገሎችና የፈረሰኞች አለቆች ተከታተሉት።


እነርሱም፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋራ ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያ ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው።


ዓይንን፣ ዩጣንና ቤትሳሚስን ከነመሰማሪያቸው ሰጧቸው፤ እነዚህ ዘጠኙ ከተሞች ከሁሉ ነገዶች ይዞታ ላይ ተከፍለው የተሰጡ ናቸው።


የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?


እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው።


እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው።


ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን ይዘው እምቧ እምቧ እያሉ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሳሚስ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዦችም እስከ ቤትሳሚስ ድንበር ተከተሏቸው።


ፈርዖን ችግሩ ጋብ ማለቱን ባየ ጊዜ ግን ልክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ልቡን በማደንደን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም።


ቤንጼቄር፣ በማቃጽ፣ በሻዓልቢም፣ በቤትሳሚስ፣ በኤሎንቤትሐናን፤


ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአስ አደጋ ጣለ። እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ በይሁዳ ምድር በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተጋጠሙ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements