Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 27:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ ነገር ግን በጎችንና ላሞችን፣ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አንኩስም ተመለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አኪሽም ይዞ ተመለሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ወንዶችንም ሴቶችንም ሁሉ እየገደለ፥ በጎችን የቀንድ ከብቶችን፥ አህዮችን፥ ግመሎችንና ልብሱንም ሁሉ ይወስድ ነበር፤ ከዚያም በኋላ ዳዊት ወደ አኪሽ ተመለሰ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዳዊ​ትም ሀገ​ሪ​ቱን መታ፤ ወን​ድም ሆነ፥ ሴትም ሆነ፥ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም፤ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ አህ​ያ​ዎ​ች​ንና ግመ​ሎ​ችን፥ ልብ​ስ​ንም ማረከ፤ ተመ​ል​ሶም ወደ አን​ኩስ መጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዳዊትም ምድሪቱን መታ፥ ወንድ ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም፥ በጎችንና ላሞችን አህያዎችንና ግመሎችን ልብስንም ማረከ፥ ተመልሶም ወደ አንኩስ መጣ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 27:9
9 Cross References  

አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንና ሴቱን፣ ልጁንና ሕፃኑን፣ የቀንድ ከብቱንና በጉን፣ ግመሉንና አህያውን ግደል።’ ”


ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከኤውላጥ አንሥቶ በምሥራቅ ግብጽ እስካለው እስከ ሱር ድረስ ወጋቸው።


በከተማዪቱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፣ ማለትም ወንዱንና ሴቱን፣ ወጣቱንና ሽማግሌውን፣ ከብቱንና በጉን እንዲሁም አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።


ከዚያም ሙሴ እስራኤልን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ፤ ለሦስት ቀናት ውሃ ሳያገኙም በምድረ በዳ ተጓዙ።


ዘሮቹም መኖሪያቸውን ከግብጽ ድንበር አጠገብ፣ ወደ አሦር በሚወስደው መንገድ፣ በኤውላጥና በሱር መካከል አደረጉ፤ ከወንድሞቻቸውም ሁሉ ጋራ በጠላትነት ኖሩ።


የእግዚአብሔር መልአክ አጋርን በአንድ የውሃ ምንጭ አጠገብ በምድረ በዳ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ዳር ነበር።


የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።


ሀብቱም ሰባት ሺሕ በጎች፣ ሦስት ሺሕ ግመሎች፣ ዐምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና ዐምስት መቶ እንስት አህዮች ነበረ፤ እጅግ ብዙ ባሮችም ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ከሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements