Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 97:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አምላክ ሆይ! ስለ ትክክለኛ ፍርድህ የጽዮን ሕዝብ ደስ ይላቸዋል፤ የይሁዳ ከተሞችም ሐሤት ያደርጋሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ወን​ዞ​ችም በአ​ን​ድ​ነት በእጅ ያጨ​ብ​ጭቡ፥ ተራ​ሮች ደስ ይበ​ላ​ቸው፥

See the chapter Copy




መዝሙር 97:8
13 Cross References  

ፍርድህ ትክክለኛ ስለ ሆነ በጽዮን የሚኖሩ ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ሐሴት ያደርጋሉ።


ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!


ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።


እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ እንዲህ ብሎ ያውጃል፦ “አዳኝሽ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር ለሰዎች የሚከፍለው ዋጋና ሽልማት አለ ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሩአት።”


“እኔ እግዚአብሔር ጽዮንንና ባድማ የሆኑባትን ቦታዎችዋን ሁሉ አጽናናለሁ፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔደን፥ በረሓዋንም እንደ ገነት አደርጋለሁ፤ በእርስዋም ተድላና ደስታ ይገኛል፤ እንዲሁም የምስጋና መዝሙር ድምፅ ይሰማል።


ኃጢአተኞችን ሲበቀልላቸው በማየታቸው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፤ በክፉዎችም ደም እግሮቻቸውን ይታጠባሉ።


የእግዚአብሔር ሰዎችም ይህን አይተው ይፈራሉ፤ እንዲህ እያሉ ይሳለቃሉ፤


እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በዓለም ሁሉ ነው።


ተሰልፋችሁ ጽዮንን ዙሩአት፤ ማማዎችዋንም ቊጠሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements