Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 83:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በሕዝብህ ላይ በስውር ያደባሉ፤ አንተ በምትጠብቃቸው ላይ ያሤራሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤ በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወፍ ለእ​ር​ስዋ ቤትን አገ​ኘች፥ ዋኖ​ስም ጫጩ​ቶ​ች​ዋን የም​ታ​ኖ​ር​በት ቤት አገ​ኘች፤ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ንጉ​ሤም አም​ላ​ኬም ሆይ፥ እርሱ መሠ​ዊ​ያህ ነው።

See the chapter Copy




መዝሙር 83:3
12 Cross References  

ከክፉዎች ምሥጢራዊ ሤራና ከክፉ አድራጊዎች ዕቅድ ጠብቀኝ።


በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል።


ከሚያሤሩባቸው ሰዎች በመኖሪያህ ጥላ ሥር ትደብቃቸዋለህ፤ ከመርዘኛ አንደበትም በከለላህ ትጠብቃቸዋለህ።


መጠለያ በመፈለግ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ፥ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መጠጊያ የሚያደርግ፥


ተሰባስበው ይሸምቁብኛል፤ እርምጃዬን ሁሉ ይከታተላሉ፤ ሕይወቴንም ለማጥፋት ያደባሉ።


እርሱም እንደ አንበሳ ተደብቆ ይቈያል፤ ድኾችን ለመያዝ ይሸምቃል፤ እነርሱንም በአሽክላው ይዞ ይጐትታቸዋል።


እናንተ በሞት የመለየትን ያኽል ከዚህ ዓለም ተለይታችኋል፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሮአል።


ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ፍልስጥኤማውያን ቊጥጥር ያደርጉባቸው ስለ ነበር በዚያን ዘመን በእስራኤል ብረት አቅልጠው የሚሠሩ ጠቢባን አልነበሩም፤


ከዚህም የተነሣ ከጠላቶቻችን ጋር ተባብረው ከወጉን በኋላ ከአገሪቱ አምልጠው መሄድ ይችላሉ፤ ስለዚህ ቊጥራቸው እየበዛ እንዳይሄድ ኑ፤ አንድ ዘዴ እንፈልግ።”


አሕዛብ ስለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements