Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 82:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ደካሞችንና ችግረኞችን አድኑ፤ ከክፉዎችም ጥቃት አስጥሉአቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወገን የሌለውንና ድኻውን ታደጉ፤ ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፥ ከክፉዎችም እጅ አስጥሉአቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “ኑ ከሕ​ዝብ ለይ​ተን እና​ጥ​ፋ​ቸው፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ስም አያ​ስቡ” አሉ።

See the chapter Copy




መዝሙር 82:4
8 Cross References  

ይህም የሆነው የድኾችን ጩኸት ሰምቼ እታደጋቸውና፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውንም ልጆች እረዳቸው ስለ ነበረ ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! ለድኾች እንደምትፈርድ፥ ለተጨቈኑትም መብታቸውን እንደምታስከብር ዐውቃለሁ።


“እኔ እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድና እውነት የሆነውን ነገር እንድታደርጉ አዛችኋለሁ፤ አንዱ ሌላውን በመቀማት ግፍ እንዳይሠራ ጠብቁ፤ መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አታንገላቱ፤ በዚህም በተቀደሰ ስፍራ የንጹሕ ሰው ደም አታፍስሱበት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements