Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 82:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር በሰማያዊው ጉባኤ አማልክት ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ በመካከላቸው ተገኝቶ ፍርድ ይሰጣል፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤ በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አት​በል፥ ቸልም አት​በል።

See the chapter Copy




መዝሙር 82:1
12 Cross References  

እንግዲህ ቅዱስ መጽሐፍን መሻር አይቻልም፤ የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን ቅዱስ መጽሐፍ አማልክት ብሎ ከጠራቸው


እግዚአብሔር በፍርድ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል፤ በሕዝቡም ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅቶአል።


በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።


በዚያን ጊዜ ሰዎች “ጻድቃን የመልካም ሥራቸውን ዋጋ አገኙ፤ በዓለም ላይ የሚፈርድ አምላክ በእርግጥ አለ” ይላሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ በመላእክት ፊት ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።


“በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል አትናገር፤ የሕዝብህንም መሪ አትስደብ።


ጌታው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ወደ ሆኑ ፈራጆች ዘንድ ይውሰደው፤ እዚያም ከበር ወይም ከበር መቃን አጠገብ አቁሞ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም በኋላ እስከ ዕድሜ ልኩ ድረስ ባርያ ሆኖ ያገልግለው።


በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።


ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥ በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል።


አይደለም! በልባችሁ ክፉ ነገርን ታቅዳላችሁ፤ በምድር ላይ የምትፈጽሙትም ሁሉ የዐመፅ ሥራ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements