Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 80:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ለኤፍሬም፥ ለብንያምና ለምናሴ ራስህን ግለጥ፤ ኀይልህን አነሣሥተህ መጥተህ አድነን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ። ኀይልህን አንቀሳቅስ፤ መጥተህም አድነን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ብርሃንህን አብራ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዝማ​ሬ​ውን አንሡ ከበ​ሮ​ው​ንም ስጡ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በገና ከመ​ሰ​ንቆ ጋር፤

See the chapter Copy




መዝሙር 80:2
14 Cross References  

ጌታዬና አምላኬ ሆይ! ተነሥተህ ተከላከልልኝ፤ ተነሥተህም ፍረድልኝ።


እግዚአብሔር ዳኛችን፥ ሕግ ሰጪአችንና ንጉሣችን ነው፤ የሚያድነንም እርሱ ነው፤


ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።


ሆኖም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምሕረትን አደረገ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር አላቸው እንጂ አላጠፋቸውም። ብዙ ጊዜ ቊጣውን መለሰ፤ ብዙ ጊዜም መዓቱን ገታ።


እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ በመክደኛው ላይ በተሠሩት ክንፍ ባላቸው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ ለእስራኤል ሕዝብ የምታቀርበውን ትእዛዞቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ።


ስለዚህም ወደ ሴሎ መልእክተኞች ልከው በታቦቱ ላይ ባሉ ኪሩቤል ዙፋኑን ያደረገ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግርማውን የሚገልጥበትን የቃል ኪዳኑን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስም የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው መጡ።


ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደስ በማግባት በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፍ ሥር አኖሩት።


እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤


እግዚአብሔር በውበትዋ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን ከተማ የደመቀ ብርሃንን ያበራል።


እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋኑ ተቀመጠ፤ ምድርም ትናወጥ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements