Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 71:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአንተ ላይ እታመናለሁ፤ ከእናቴ ማሕፀን እንድወለድ ያደረግኸኝ አንተ ነህ፤ እኔም ዘወትር አመሰግንሃለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤ አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እንደ ጠል በባ​ዘቶ ላይ፥ በም​ድ​ርም ላይ እን​ደ​ሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ጠብታ ይወ​ር​ዳል።

See the chapter Copy




መዝሙር 71:6
16 Cross References  

“ኤርምያስ ሆይ! ገና በእናትህ ማሕፀን እንድትፀነስ ከማድረጌ በፊት ዐውቄሃለሁ፤ ከመወለድህም በፊት አንተን በመለየት ለሕዝቦች ነቢይ አድርጌ ሾሜሃለሁ።”


ነገር ግን ከመወለዴ በፊት እግዚአብሔር መረጠኝ፤ በጸጋውም ጠራኝ።


ገና በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር መርጦኛል፤ የተበታተኑትን የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን ለመሰብሰብ አገልጋዩ አድርጎኛል። እኔ በእግዚአብሔር ዘንድ የተከበርኩ ነኝ፤ አምላኬም ኀይል ሆኖልኛል።


በደሴት የምትኖሩ ሕዝቦች አድምጡኝ! በሩቅ አገር ያላችሁም ሰዎች አስተውሉ፤ እግዚአብሔር ከመወለዴ በፊት ጠራኝ፤ በእናቴ ማሕፀን እያለሁ ስም አወጣልኝ።


ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር በአንደበቴ ነው።


“አሁን ‘አባቴ፥ የልጅነት ጓደኛዬ’ ብለሽ አልጠራሽኝምን?


እኔ የሚወዱኝን እወዳለሁ፤ የሚፈልጉኝም ያገኙኛል።


እኔ ግን ዘወትር አንተን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በበለጠም መላልሼ አመሰግንሃለሁ።


በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር አብን ዘወትር አመስግኑ።


መከራ ሊደርስብኝ ስለ ተቃረበና የሚረዳኝም ስለሌለ እባክህ ከእኔ አትራቅ!


በእግዚአብሔር ብቻ የሚታመኑ፥ ወደ ጣዖቶች የማይመለሱ፥ ሐሰተኞች አማልክትን ከሚከተሉ ከዐመፀኞች ሰዎች ጋር የማይተባበሩ የተባረኩ ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements