Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 69:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጒር ይልቅ በዝተዋል፤ ብዙዎች ጠላቶቼ ሊያጠፉኝ ይፈልጋሉ ያልሰረቅኹትን ነገር መመለስ አለብኝን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣ በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ ያልሰረቅሁትን ነገር፣ መልሰህ አምጣ ተባልሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በጩኸት ደከምሁ ጉሮሮዬም ሰለለ፥ አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አቤቱ፥ የሚ​ሹህ ሁሉ በአ​ንተ ሐሤት ያድ​ርጉ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤ ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወ​ድዱ፥ “ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።

See the chapter Copy




መዝሙር 69:4
14 Cross References  

ይህም የሆነው፥ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።


ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ምክንያት እንዲደሰቱ አታድርግ፤ በኋላዬ ሆነው እንዲጠቃቀሱብኝም አታድርግ።


እኛ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋዮች እንድንሆን እግዚአብሔር ኃጢአት የሌለበትን ክርስቶስን የእኛን ኃጢአት እንዲሸከም አደረገው።


ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።


ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።


እርሱ ምንም ኃጢአት አላደረገም፤ በአፉ ተንኰል አልተገኘበትም።


እንዴት እንደ ሸመቁብኝ ተመልከት! እግዚአብሔር ሆይ! ምንም በደልና ኃጢአት ሳልሠራ ዐመፀኞች ሰዎች በእኔ ላይ ያሤራሉ።


ከኃጢአት ተለይተን በጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።


ከጠላቶቼ ተቃውሞ የተነሣ በጣም በማልቀሴ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ ማየትም ተስኖኛል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements