Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 69:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የአገልጋዮቹም ዘሮች ይወርሱአታል፤ እርሱን የሚወዱ ሁሉ እዚያ ይኖራሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 የባሪያዎቹም ዘሮች ይወርሷታል፤ ስሙንም የሚወድዱ በዚያ ይኖራሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥ የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና፥ በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሱአትማል።

See the chapter Copy




መዝሙር 69:36
13 Cross References  

የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ፤ ትውልዳቸውም በአንተ ዘንድ ጸንቶ ይኖራል።


የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፥ ጌታ አምላካችን ወደ እርሱ ለሚጠራቸው፥ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነው።”


ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ።


ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ እኛ ወደ እርሱ መጥተን ከእርሱ ጋር አብረን እንኖራለን።


ጌታ በቃል ኪዳኑ መሠረት ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የሕይወት አክሊል ስለሚቀበል ፈተናን ታግሦ የሚጸና ሰው የተባረከ ነው።


እግዚአብሔርን ለሚወዱና እንደ ፈቃዱም ለተጠሩት ሰዎች እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለበጎ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።


ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለሚወደኝ ከጠላቶቹ እጅ አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም ስለሚያውቅ እጠብቀዋለሁ።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements