Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 68:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ብዙ ዝናብ እንዲዘንብ አደረግህ፤ ያረጀውን መሬትህን አደስህ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር ሆይ፣ በቂ ዝናብ አዘነብህ፤ ክው ብሎ የደረቀውን ርስትህን አረሰረስህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠባጠቡ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የቤ​ትህ ቅን​ዓት በል​ቶ​ኛ​ልና፥ የሚ​ሰ​ድ​ቡ​ህም ስድብ በላዬ ወድ​ቆ​አ​ልና።

See the chapter Copy




መዝሙር 68:9
10 Cross References  

ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር የክረምቱንና የበልጉን ዝናብ በወቅቱ ለምድራችሁ ይልካል፤ በዚህም ዐይነት ለእናንተ ሲሳይ የሚሆነው እህል፥ ወይን ጠጅና የወይራ ዘይት፥


“እነርሱንና በተራሮቼ አካባቢ ያሉትን ቦታዎች እባርካለሁ፤ ዝናቡንም በወቅቱ አዘንባለሁ፤ እርሱም የበረከት ዝናብ ይሆናል።


እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።


እግዚአብሔር ሆይ! ከኤዶም ተራራ በተነሣህ ጊዜ፥ በኤዶምም ምድር ላይ በተራመድህ ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያት ዝናብን አዘነቡ፤ አዎ! ውሃ ከደመናዎች ወደታች ጐረፈ።


በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፥ በሲናው አምላክ ፊት፥ ተራራዎች ተናወጡ።


እግዚአብሔርም ኤልያስን “ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም” አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኰረቶችን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድሪቱ ነውጥ ውስጥ አልነበረም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements