Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 57:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ነፍሴ ሆይ! ተነሺ፤ በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ! እኔም በማለዳ እነሣለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ነፍሴ ሆይ፤ ንቂ! በገናና መሰንቆም ተነሡ! እኔም ማልጄ እነሣለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ ሰም ያል​ቃሉ፤ እሳት ወደ​ቀች፥ ፀሐ​ይ​ንም አላ​የ​ኋ​ትም።

See the chapter Copy




መዝሙር 57:8
11 Cross References  

ስለዚህ ልቤ ተደስቶ ይፈነጥዛል፤ ሰውነቴም ያለ ስጋት ያርፋል።


ስለዚህ ዝም አልልም፤ ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ስለዚህ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።


ዲቦራ ሆይ! ንቂ! ንቂ! ንቂ! መዝሙርም ዘምሪ! የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ሆይ! ተነሣ! ምርኮህንም እየመራህ ወደ ፊት ገሥግሥ!


ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ አንደበቴም በደስታ ተሞላ፤ እንዲሁም ሟች የሆነው ሥጋዬ በተስፋ ይኖራል፤


ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም።


እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል ኢየሩሳሌምንም ይታደጋል ስለዚህ እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ! ተባብራችሁ በደስታ ዘምሩ።


በመለከት አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።


ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም በእምቢልታ፥ በዋሽንትና በበገና ድምፅ እየታጀቡ በሰልፍ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ፤


አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።


አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements