Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 51:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከተፀነስኩበት ጊዜ ጀምሮ ኀጢአተኛ ነኝ፤ ከተወለድኩበትም ጊዜ ጀምሮ በደለኛ ነኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስወለድ ጀምሮ በደለኛ፣ ገና እናቴም ስትፀንሰኝ ኀጢአተኛ ነኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያፈ​ር​ስ​ሃል፤ ከቤ​ት​ህም ይነ​ቅ​ል​ሃል፥ ያፈ​ል​ስ​ሃ​ልም፥ ሥር​ህ​ንም ከሕ​ያ​ዋን ምድር።

See the chapter Copy




መዝሙር 51:5
9 Cross References  

በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአት ምክንያትም ሞት መጣ፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ኃጢአትን ስለ ሠራ ሞት በሰው ሁሉ ላይ መጣ፤


ክፉዎች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ በድለዋል፥ ሐሰትንም ተናግረዋል።


ከርኩስ ነገር ንጹሕ ነገርን ማግኘት የሚችል ከቶ ማንም የለም።


እኛም ሁላችን ከዚህ በፊት በእነርሱ መካከል የሥጋችንን ፈቃድና የአእምሮአችንን ሐሳብ እየተከተልን በሥጋችን ምኞት እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም በተፈጥሮአችን በእግዚአብሔር ቊጣ ሥር ነበርን።


ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው።


አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልኩና በአምሳያው እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ሤት” የሚል ስምም አወጣለት።


የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።


ሴትና ወንድ አብረው ተኝተው በሚነሡበት ጊዜ፥ ሁለቱም ሰውነታቸውን በውሃ ታጥበው እስከ ምሽት ድረስ የረከሱ ይሆናሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements