Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 45:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ልቤ መልካም ርእስን ያፈልቃል፤ ጽሑፌም የሚያተኲረው በንጉሡ ላይ ነው፤ አንደበቴም እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ፤ የተቀኘሁትን ቅኔ ለንጉሥ አሰማለሁ፤ አንደበቴም እንደ ባለሙያ ጸሓፊ ብርዕ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት፥ የፍቅር መዝሙር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አም​ላ​ካ​ችን መጠ​ጊ​ያ​ች​ንና ኀይ​ላ​ችን ነው፤ ባገ​ኘን በታ​ላቅ መከ​ራም ጊዜ ረዳ​ታ​ችን ነው።

See the chapter Copy




መዝሙር 45:1
23 Cross References  

አንደበቴ የጥበብ ቃላትን ይናገራል፤ የልቤ ሐሳብም ማስተዋልን ያስገኛል።


ቃሎቼ የልቤን ቅንነት ይገልጣሉ፤ ምላሶቼም እውነቱን ይናገራሉ።


የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ አማካይነት ይናገራል፤ ቃሉም በአንደበቴ ነው።


የጥበበኛ ሰው አእምሮ ንግግሩን ይቈጣጠራል፤ ከአፉም የሚወጣው ንግግር ትምህርትን ያስፋፋል።


ማንኛውም ትንቢት በሰው ፈቃድ ከቶ አልመጣም፤ ነገር ግን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተቀብለው የተናገሩት ነው።


ስለ ወይኑ ተክል ለውዴ የፍቅር ዘፈን ልዝፈን ውዴ እጅግ ለም በሆነ ኰረብታ ላይ የወይን ተክል ነበረው።


የውሃ ሙላት እስከ አንገቴ ስለ ደረሰ፤ አምላክ ሆይ! አድነኝ!


ትክክለኛ የሆነውን ነገር መርምረን እንወቅ፤ መልካሙንም ነገር አብረን እንማር።


ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፤ ይህንንም የምለው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ ነው።


የተከሰሰበትንም ወንጀል የሚያመለክት፥ “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ነው?” የሚል ጽሑፍ በመስቀሉ ራስጌ ላይ አኖሩ።


ንጉሡ በድንክ አልጋው ላይ ዐረፍ ብሎ ሳለ የሽቶዬ መዓዛ ቤቱን ሁሉ ሞላው።


“በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ ንጉሤን ሾምኩ” ይላቸዋል።


ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ ሊቅ ነበር፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!


“መልካም ሰው ከመልካም መዝገቡ፥ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገቡ ክፉ ነገርን ያወጣል።


የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።


አምላክ ሆይ! ዋላ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements