Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 38:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በደሌ በራሴ ላይ ተጭኖአል፤ እርሱም ለመሸከም ከምችለው በላይ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በደሌ ውጦኛል፤ እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከቁጣህ የተነሣ ሥጋዬ ጤና የለውም፥ ከኃጢአቴም የተነሣ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥ የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?

See the chapter Copy




መዝሙር 38:4
9 Cross References  

ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።


“አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ስለ ሆነና በደላችንም ወደ ሰማይ ስለ ደረሰ ፊቴን ወደ አምላኬ ወደ አንተ ለማቅናት ዐፍራለሁ እፈራለሁም።


“እናንተ በጉልበት ሥራ የደከማችሁ! ሸክምም የከበደባችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ! እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።


ከኃጢአት ተለይተን በጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።


“በደሎቼ በጫንቃዬ ላይ ታስረዋል፤ እነርሱም በጣም ከባድ ስለ ሆኑ ኀይል አሳጡን፤ ልንቋቋማቸው ለማንችላቸው ጠላቶቻችን አሳልፎ ሰጠን።


ጻድቁ አገልጋዬ ከሥቃዩ በኋላ የሕይወትን ብርሃን አይቶ ይረካል፤ በዕውቀቱም ብዙዎችን ያጸድቃል፤ በደላቸውንም ይሸከማል።


ከተረፈው ሥጋ ምንም ያኽል በሦስተኛው ቀን ቢበላ የዚያን ሰው መሥዋዕት እግዚአብሔር አይቀበልለትም፤ መሥዋዕቱም እንደ ቀረበ ሆኖ አይቈጠርለትም፤ እንዲያውም እንደ ረከሰ ሆኖ ይቈጠራል፤ እርሱንም የበላ ሰው የበደሉን ፍዳ ይቀበላል።


ወይም እንደገና ሰው በአጥንቱ ውስጥ በማያቋርጥ በሽታ በአልጋ ቊራኛነት እንዲገሠጽ ያደርጋል።


የዐመፅን መንገድ በመከተላቸው አንዳዶቹ ሞኞች ነበሩ ሕግን በመተላለፋቸው ምክንያት ተቀጥተውበታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements