Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 31:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አንተ መጠጊያዬ ስለ ሆንክ ጠላቶቼ ከዘረጉብኝ ወጥመድ አውጣኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አንተ መጠጊያዬ ነህና፣ በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አምባዬና መጠጊያዬ አንተ ነህና ስለ ስምህ መንገዴን አቅና ምራኝም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በቀ​ንና በሌ​ሊት እጅህ ከብ​ዳ​ብ​ኛ​ለ​ችና፥ እሾህ በወ​ጋኝ ጊዜ ወደ ጕስ​ቍ​ልና ተመ​ለ​ስሁ።

See the chapter Copy




መዝሙር 31:4
11 Cross References  

ከወጥመዶች ሁሉ ስለሚያድነኝ ሁልጊዜ ወደ እርሱ እመለከታለሁ።


ትምክሕተኞች ወጥመድ ዘረጉብኝ፥ እንደ መረብ የተጠላለፈ ገመድም ዘረጉብኝ። እኔንም ለመያዝ በመንገዴ ላይ ወጥመድ አጠመዱ።


በዚህ ዐይነት ወደ ልቡናቸው ተመልሰው ዲያብሎስ ፈቃዱን እንዲፈጽሙ እነርሱን ከያዘበት ወጥመድ ያመልጣሉ።


ጠላቶቼ እኔን ለመያዝ ወጥመድ ዘርግተውብኛል፤ ሁለንተናዬን የሚያጐብጥ ተስፋ መቊረጥ ደረሰብኝ፤ በመንገዴ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ወደቁበት።


አምባዬና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ! ቃላቴና ሐሳቦቼ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው።


ወዳጆቹን የሚያቈላምጥ ሰው ለእግራቸው ወጥመድ ይዘረጋል።


እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አምልጠናል፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም ነጻ ወጣን።


ያለ ምክንያት ወጥመድ በድብቅ ዘርግተውብኛል፤ እኔንም ለመያዝ ጒድጓድ ቆፍረዋል።


ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።


ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ እርሱም ከጠላቶቼ ያድነኛል።


ሕይወቴን ያድሳል፤ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements