Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 30:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ሆይ! ሞገስን በሰጠኸኝ ጊዜ እንደማይነቃንቅ ተራራ አበረታኸኝ፤ ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተስፋ ቈረጥኩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ ተራሮቼ ጸኑ፣ ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ ውስጤ ታወከ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በት​ድ​ግ​ናህ ደስ ይለ​ኛል፤ ሐሴ​ትም አደ​ር​ጋ​ለሁ። መከ​ራ​ዬን አይ​ተ​ሃ​ልና፥ ነፍ​ሴ​ንም ከጭ​ን​ቀት አድ​ነ​ሃ​ታ​ልና።

See the chapter Copy




መዝሙር 30:7
16 Cross References  

አንተ ስትለያቸው ሁሉም ይደነግጣሉ፤ እስትንፋሳቸውን ስትወስድባቸውም ይሞታሉ፤ ወደ ተገኙበትም ዐፈር ይመለሳሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ።


ገናናው ኀይልህ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ በቸርነትህም ብርታታቸው እያደገ ይሄዳል።


ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤ እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።


እርሱ የሚቈጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን ለዘለዓለም ነው፤ ሌሊት ሲለቀስ ዐድሮ በማለዳ ደስታ ይሆናል።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ጻድቃንን ትባርካለህ፤ በቸርነትህም እንደ ጋሻ መከላከያ ትሆንላቸዋለህ።


ሕይወትንና ዘለዓለማዊ ፍቅርን ሰጥተኸኛል፤ ጥበቃህም መንፈሴን አጸናው።


ይህም በሚሆንበት ጊዜ እኔ በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ እለያቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይደመሰሳሉ፤ በእነርሱም ላይ ብዙ አሠቃቂ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ፥ ‘ይህ ችግር የመጣብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደለምን?’ ይላሉ።


ችግር የደረሰብኝ በእርግጥ ለደኅንነቴ ነው፤ ከአደጋም ሁሉ ሕይወቴን ታድናለህ፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር ትላለህ።


ይህም የሆነው ከፍ ከፍ ካደረግኸኝ በኋላ፥ ከኀይለኛ ቊጣህ የተነሣ ስለ ጣልከኝ ነው።


እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለምን እንደዚህ ርቀህ ትቆማለህ? በችግር ጊዜስ ስለምን ትሰወራለህ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements