Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህ በኋላ በቊጣው ይገሥጻቸዋል፤ በመዓቱም ያስፈራራቸዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም በቍጣው ይናገራቸዋል፤ በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በዚያን ጊዜ በቁጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በዚ​ያን ጊዜ በቍ​ጣው ይና​ገ​ራ​ቸ​ዋል፥ በመ​ዓ​ቱም ያው​ካ​ቸ​ዋል።

See the chapter Copy




መዝሙር 2:5
15 Cross References  

ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።


ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ በብረት በትርም ይገዛቸዋል፤ እርሱ ሁሉን የሚችለውን የእግዚአብሔር አስፈሪ ቊጣ መግለጫ የሆነውን የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል፤


በምትገለጥበት ጊዜ ከምድጃ እንደሚወጣ የእሳት ነበልባል ታቃጥላቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በቊጣው ወላፈን ይለበልባቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል።


በእነርሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ግን እዚህ አምጥታችሁ በፊቴ ግደሉአቸው!’ ” አላቸው።


ሰላም አግኝተው በጸጥታ በሚኖሩ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እጅግ ተቈጥቼአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሕዝቤን ከመቅጣት መለስ ባልኩበት ጊዜ እነዚያ የአሕዛብ መንግሥታት ሕዝቤን ከተጠበቀው በላይ አሠቃይተዋል።


በከተማ የሚሰማውን ሁካታ አድምጡ! ከቤተ መቅደስም ድምፅ ስሙ፤ ይህም እኔ እግዚአብሔር ለጠላቶቼ ተገቢ ዋጋቸውን በምሰጥበት ጊዜ የሚሰማ ድምፅ ነው።”


በቀኝ እጁ ሰባት ኮከቦችን ይዞ ነበር፤ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ከአፉ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበረ።


በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቈጣና ወታደሮቹን ልኮ እነዚያን ገዳዮች አስገደለ፤ ከተማቸውንም በእሳት እንዲያቃጥሉ አደረገ፤


እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ሁሉ ክፉ ነገር በእኔ ላይ የሚናገሩትን ጠላቶቼን በዚህ ዐይነት ቅጣቸው።


እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ላይ ተቈጥቶአል፤ ኀይለኛ ቊጣውም በሠራዊቶቻቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ፈጽሞ ያጠፋዋል፤ በሰይፍም እንዲገደሉ አሳልፎ ይሰጣቸዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements