Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 18:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ እጁን በመዘርጋት ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አቤቱ፥ ከዘለፋህ ከአፍንጫህ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።

See the chapter Copy




መዝሙር 18:16
10 Cross References  

እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ እጁን በመዘርጋት ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ።


እጅህን ከላይ ስደድ፤ ከጥልቅ ውሃ ውስጥ ስበህ አውጣኝ፤ ታደገኝም፤ ከባዕዳን ኀይል አድነኝ።


እግዚአብሔር ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤ የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገልጣል።


ከዐመፀኛ ሕዝብ አዳንከኝ፤ በአሕዛብም ላይ ሾምከኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ይገዛልኛል።


ሕፃኑም ባደገ ጊዜ ወደ ንጉሡ ልጅ አመጣችው፤ የእርስዋም ልጅ ተባለ። እርስዋም “ከውሃ ያወጣሁት ስለ ሆነ ስሙ ሙሴ ተብሎ ይጠራ” አለች።


መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራይቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ሕዝቦችና፥ ሰዎች፥ ወገኖችና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ናቸው፤


ስለዚህ በጭንቀት ሰዓት እያንዳንዱ ለአንተ ታማኝ ሰው ወደ አንተ ይጸልይ፤ ብርቱ የመከራ ጐርፍ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን አይነካውም።


እግዚአብሔር ባሕሩንና ወንዞቹን ገሥጾ ያደርቃቸዋል። በባሳንና በቀርሜሎስ የሚገኙ ዕፀዋት ይደርቃሉ፤ የሊባኖስም አበቦች ይጠወልጋሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements